የስርዓተ-ምህዳር ጥቅሞችና ስጋቶቻቸው
የባህር ላይ አዝመራ © አናቶክ ሊሚትድ
ለተፈጥሮ ዋጋ የምትሰጠው ለምንድን ነው? ልክ በጥቂት ሀገራት ውሰጥ ባሉ ገጠራማ አካባቢዎች እንደሚኖሩ ሰዎች የገቢ ምንጫችን የምናገኘው ከተፈጥሮ ስለሆነ? ፍራፍሬዎችን፣ ፈንገሶችን ከጫቃ መልቀም ወይም ደግሞ አሶችን ማጥመድ አልያም በተለያዩ መንገድ እንስሳቶችን ማደንስ ይወዳሉ? በአንድ አንድ ሀገራት ምግባቸውን በብዛት የሚያገኙት ከሱቆች ቢሆንም በአጠቃላይ አንድ ሶስተኛው የሚሆነው ሰው ምግባቸውን ከተፈጥሮ የመሰብሰብ ጠንካራ የሆነ ልማድ አላቸው፡፡ ምንአልባት እናንተ ደግሞ የዱር-ህይወትን በመመልከት ከጭንቀታቹ ማረፍና አንዳንድ እንቅስቃሴዎች ማድረግ ያሰደስታቹ ይሆናል? እንዲያ ከሆነ እርስዎ ፍሬያማና ባህላዊ የምንለውን የስርዓተ-ምህዳር ጥቅሞችንና አገልግሎቶችን እያገኛቹ ነው፡፡ ሰደድ እሳት፣ ጎርፍ እና የሰብሎቸ በዋግ መመታት እነዚህ ሁሉ ደግሞ የስርዓተ-ምህዳር አገልግሎቱ ሲጎዳ የሚከሰቱ ችግሮች ናቸው፡፡ ስለዚህ ሁላችንም የምንተነፍሰውን አየር፣ ንፁህ ውኃ እና የአየር ንብረት የምናግኘው ስርዓተ-ምህዳር ሂደት ውስጥ ነው፡፡
ሰዎች በስርዓተ-ምህዳር ላይ የሚያደርሱት ተፅዕኖ
ኢንዱስትሪ አየርን፣ አፈርን እና ውኃን ሊበክል ይችላል© ሂሞቪክ / ሹትቶቶክ
ስርዓተ-ምህዳሮችን ለራሳችን ጥቅም ባማከለ መንገድ ስናሻሽላቸው አስከፊ ጉዳት ሊያደርሱ ይችላሉ፡፡ ይኸውም በጣም ለም፣ ሳራማ፣ ደናማ እና ረግረጋማ ቦታዎች ላይ ለተለያዩ ሀገር በቀል ዝርያዎች ጠቃሚ የሆኑ እፅዋቶችን በማስወገድ የአፈርን ለምነት በሚቀንሱ አንድ ወይም ጥቂት ሰብል ወደሚዘራበት የእርሻ መሬት ሊለወጡ ይችላሉ፡፡ ለእርሻ በማይመቹ ቦታዎች ደግሞ አዳኝ የዱር እንስሳ ከአካባቢው ተወግደው በግጦሽ መሬት ላይ ትልቅ ጫና በማድረስ የቤት እንስሳቶች በዱርህይወት ሊተኩ ይችላሉ፡፡ በተወሰነ ለም ናቸው በሚባሉ ወይም በቀላል ተደራሽነት ባላቸው ረግረጋማና በረሃማ ቦታዎች ላይ ደግሞ የቱሪዝም ስብህት በመጨመር አካባቢው የተፈጥሮ ይዘቱን የሚያስለቅቁ አሉታዊ ተፅዕኖዎች ሊፈጠሩ ይችላሉ፡፡ የአካባቢው ማኅበረሰብና ቱሪስቱ ሆን ብሎ ተጽዕኖ ባያሳድርም በአለማችን የሚለቀቁ ፕላሰቲኮች፤ ውኃንና አየርን የሚበክሉ ነገሮች ሁሉ ጉዳታቸው ርቀው ወደሚገኙ አካባቢዎች እንኳ ሳይቀር ይደርሳሉ ። ሌሎች በሰፊው የተስፋፋ ችግሮች ደግሞ ሳናውቅ በሽታዎችን በማስተላለፍና በአካባቢው ከሚኖሩ ህያዋን ፍጥረታት ይበልጥ ጠንካራ የሆኑ ሌሎች ህያዋን ፍጥረታትን ወደ አዲስ ስፍራ በማምጣት ነው። እነዚህ ሁሉ ችግሮች ስነምህዳሩ ለሰው ልጆችና አለማችንን ለምናጋራቸው ሌሎች ፍጥረታቶች የሚሰጠውን አገልግሎት እነዲቀንስ ሊያድርጉት ይችላሉ፡፡
በስርዓተ-ምህዳሩ ላይ የሚያደርሱት የሰዎች ተፅዕኖ መቆጣጠር
ችግሮች በአንድ አካባቢ ላይ ሲከሰቱ የአካባቢው ነዋሪዎች ብዙ ጊዜ አስቀድመው ችግሩን ይለያሉ አልፎ አልፎም አዋጪና ቀላል በሆነ መንገድ ችግሩን ይፈቱታል፡፡ በአካባቢው ያሉ ገበሬዎችን፣ የደን ባለሙያዎች፣ ዓሣ አጥማጆችን፣ አዳኞችን፣ የዱር አራዊት ጠባቂዎችን፣ ሰብሳቢዎችንና አትክልተኞችን ጨምሮ ሥነ ምህዳራዊ አገልግሎቶችን ለማስተዳደር በሳይነቲስቶችና በመንግስት የሚታገዝ ሰፊ ክህሎቶች ያስፈልጋሉ፡፡ በቂ ጊዜና አመቺ ሁኔታዎች ከተፈጠሩ ደግሞ የስርዓተ-ምህዳሮች የተፈጥሮ ሀብት በተወሰነ መጠን ሊያገግሙና ሊታደሱ ይችላሉ፡፡ ብዙ ጊዜ አትክልት እና ትናንሽ ፍጥረታቶች እንደ ትላትል እና ሌሎች ትናንሽ እንስሳዎች በፍጥነት ሊመለሱ ይችላሉ ነገር ግን ትላልቅ ደኖችን ለመፍጠር ብዙ አስዕርተ አመታት ሲፈጁ የላይኛውን የመሬት ክፍል ለምነትን ለመመለስ ግን ብዙ መቶ አመታት ሊፈጁ ይችላሉ፡፡ እንዲህ ያለውን ስራ መስራት ለማስቻልና ለመርዳት ሳይንቲስትና መንግስት እንዴት የአካባቢውን ሰዎች ጥረተ መደገፍና ማበረታታት እንዳለባቸው መረዳት አለባቸው፡፡ የአካባቢ ሰዎች ለተፈጥሮ ሀብት ጥበቃና ልማት አስተዋፅዖ እነዲያደርጉና በዘለቄታዊ የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀም ያላቸውን እውቀት ለሌሎች እነዲያካፍሉ ማበረታታትም ይገባል፡፡