ያልተለመዱ ባህላዊ እውቀቶች ፍራንክሊን ያልታሰበውን የአርክቲክ ጉዞን ምስጢር ለመፍታት አግዘዋል© ዊኪኮመንስ
አስተዳደር ሰዎች ጉዳያቸውን የሚፈቱበት መንገድ ነው፡፡ ከታች ወደ ላይ ያለ አስተዳደር ብቻ አይደለም፡፡ ከአምባገነናዊ መንግስት ውጪ አስተዳደር በሳይንስና በልምዶች ላይ መሰረት ባደረገ እውቀት የጋራ ስምምነትን ይፈልጋል፡፡ ባህላዊ እውቀት አካባቢውን ለብዙ መቶ አመታት በሚውቁና በጠበቁ ሰዎች ለረዥም ጊዜ የተደረገን የተፈጥሮ ምልከታና ራሳቸውን ለመጥቀም ወደ አስተዳደራዊ ልምምድ በመለወጥ የሚያድግ እውቀት ነው፡፡ ይህ ሁሉ ዓቀፍ ዕውቀትን በድጋሚ ማግኘት ከባድ ስለሆነ በጣም ጠቃሚ ሀብት ነው፡፡ ምልከታዎችን በማነፃፀር ሙከራ የሚያደርገወ ዘመናዊ ሳይንስ በዚህ በሚለዋወጥ ጊዜ መረጃዎችን በፍጥነት እንዲገኝ ይረዳል፡፡ ከሌላ የተወሰደ አስተዳደር ደግሞ የቱ እነደሚሰራና እነደማይሰራ በማየት በተቀናጀ መንገድ ውሳኔዎችን ለማሳወቅ ሊረዳ ይችላል፡፡
የባህር ላይ ወፎች በብክለት፣ በአየር ንብረት ለውጥ፣ ከመጠን በላይ ዓሳ ማስገር እና በማጥመድ ምክንያት ስጋት ላይ ወድቀዋሉ © ማሪና ሮሴልስ ቤነቲስ ዲ ፍራንኮ
IUCN በዓለም-ዓቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያለው በቁጥራቸውና የመቀነስ መጠናቸው መሰረት ያደረገ ፍጥረታትን እንደየደረጃቸው የሚያስቀምጡበት ሂደት አላቸው፡፡ ይኸውም አንድ የፍጥረታት ዝርያ መቀነሱን የሚያሳይ አሳማኝ መረጃ እስከሌለ ድረስ ዝርያው ስጋት የሌለው ነው እንላለን ነገር ግን አንድ ዝርያ ካለው መንጋ ለርካቡኤ ስጋ ከደረሱት ውስጥ ከተለመደው ተፈጥሮአዊ ዑደት ሲነፃፀር ቁጥራቸው በፍጥነት በግማሽ ከቀነሰ ስጋት ላይ ናቸው እንላለን፡፡ ዝርያቸው እየቀነሰ ያለበትን ምክንያት መቀልበስ የሚቻልበት መንገድ ከተገኘ የሁሉም ዝርያዎች ነገር ግን ትላልቅ ዝርያዎች በጣም በፍጥነት በድጋሚ በእጥፍና ከዛም በላይ ሊያድጉ ይችላሉ፡፡ የፍጥረታት ቁጥር መቀነስ ሊቀለብስ የሚያስችል ሁለት ዘዴዎች በባለስልጣኑ ተገኝተዋሉ ይኸውም ቅጣትና ሽልማት ናቸው፡፡
ጥበቃና ቅጣት
የቀድሞው የዘረመል ምርመራ የደም ናሙና ይፈልግ ነበር አሁን ግን ቅንጣት የምታክል ናሙና ነው የሚያስፈልገው © አንትራክ ኤልቲዲ፡፡
IUCN ጥብቅ ቦታዎችን በተለያዩ መንገዶች ከፍለዋቸዋል ይኸውም አብዛኛው የሰዎች ልጆች እንቅስቃሴ ከሚፈቀድበት እስከ ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ ማድረግ እማይፈቀድበት ነው፡፡ የእንስሳትና ዕፅዋት ዝርያዎች ጥበቃም በጥንካሬ ከመግደል አንስቶ በሚራቡበት ወቅት መግደል እስከመከልከል ይለያያል የእንስሳ መብት ተሞጋቾችም እንስሳቶችን ዝም ብሎ እንዳይቀመጡ ይፈልጋሉ፡፡ የጥበቃ ህጎች ሰኬታማ የሚሆኑት የህዝብ ድጋፍ ካገኙ በተጨማሪም ልክ እንደ ዘረመል ምርመራ ክፍተቶች በቀላሉ ከተስተዋሉና መፍትሄ ከተበጀላቸው ነው፡፡ ነገር ግን ዝርያዎቹ በአካባቢው ማህበረሰብ ላይ ሁነኛ ጉዳት የሚያስከተሉ ከሆነና በተለይ ደግሞ ችግሮቹ የሚሸፋፈኑ ከሆነ ጥበቃው ብዙ ውጤታማ አይሆንም፡፡ ወንጀለኛን የማያስተምር ጠበቅ ያለ ክልከላና ቅጣት የአካባቢውን ማህበረሰብም ሊያሰቆጣና ሊያርቅ ይችላል፡፡
ሽልማቶች እና መልሶ ማቋቋም
በፌር ዋይልድ ኢኒሼቲቭ የዱር ዕፅዋት እውቅና መስጠት© የባህላዊ መድሃኒት ኢንክ
እንስሳቶች ችግር ሲያስከትሉ የተወሰነ አስተዳዳሪያዊ እርምጃዎችን መውሰድ የአካባቢ ሰዎች ድጋፍ ያስገኛል፡፡ ስነምህዳራዊ መስተጋብሩን ጠብቆ ማቆየትና ማደስ የረዥም ጊዜ ጥረት ይፈልጋል፡፡ ህጎች የሚፈለገውን ጥረት አያመጡም በአስተዳደሩ ላይ የሚጣሉ ክልከላዎችም ጥረቱን አያበረታቱም፡፡ ሆኖም ግን የዱር ዝርያዎች እሴት ግብርና ከሚያስገኘው ጥቅም በላይ ከሆነ በዘለቄታዊ መንገድ ይኸውም የአሁኑንና የሚመጣውን ትውልድ ፍላጎት ጠብቆ መጠቀም ካስቻለ ማህበረሰቡ ሊያለሙትና ሊጠብቁት ይችላል፡፡ ችግር የሚያስከትሉ የእንስሳ ዝርያዎችን ለመጠበቅ ጫና ከማሳደር ይልቅ ሽልማቶች የተሻለ ውጤታማ ያደርጋሉ፡፡ ስጋን መውሰድና የአደን መብትን መሸጥ ጠንካራ ሽልማት ሊሆን ይችላል፣ የዱር ህይወትን በማስጎብኘት በቱሪዝም ስነምህዳራዊ መስተጋብሩን ሳይጎዳ ጥቅም ማግኘት ይቻላል፡፡ ሌሎች ሽልማቶች ደግሞ መንግስት ልማትና ጥበቃ ላይ ለተሰማሩ ሰዎች መክፈልና ለምርጥ ተግባሮቻቸው መሸለም ናቸው፡፡ የተፈጥሮ ውጤቶችን ከብቃት ማረጋገጫ ወረቀት ጋር በመጠቀም ዘለቄታዊ በሆነ መንገድ መጠቀማቸውን ማሳየትም ጥሩ ነው፡፡ በቅርቡ በተፈጥሮ ጥበቃና ልማት ላይ የወጣው ዓለም-ዓቀፉ የብዘሀ-ህይወት ስምምነት ዘለቄታዊ አጠቃቀም የሚለው ቃል ጥበቃ ከሚለው ቃል በላይ አምስት ጊዜ ተጠቅሶዋል፡፡
ከሌላ የተወሰደ አሰተዳደር
መልካም አስተዳደር ሁኔታዎችና ማስረጃዎች ሲለወጡ ከዛ ጋር የሚሰማማ አካሄድ መቅረፅ አለባቸው፡፡ ለምሳሌ በዘለቄታው መንገድ ለመጠቀም በቂ የነበሩ ዝርያዎች ድንገት ስጋት ላይ ሊወድቁና ጥበቃ ሊያሰፈልጋቸው ይችላሉ ነገር ግን ቁጥራቸው ወደነበረበት እስኪያገግሙ ድረስ ነው ከዚያም በዘለቄታዊ መንገድ በመጠቀማችን ያገኘነው ጠቀሜታ ድጋሚ ስነምህዳራዊ መስተጋብሩን ለማልማትና ለመጠበቅ ያነሳሳል፡፡ በሌሎች አካባቢ የሚገኙ ሰዎች ያገገሙትን እንስሳ ለጥበቃ ወይም ለቱሪዝም ምልክት ከሆኑ ወይም ደግሞ በቤት ውስጥ በማራባት ፍላጎታችንን በመሙላት ገንዘብ ማግኘት ከተቻለ በድጋሚ መጠቀም የለብንም ብለው ያምናሉም ይቃወማሉም፡፡ ምናልባት የአካባቢ ሰዎች በራሳቸው አቅም ግቡን ካላሳኩ ክልከላና ጥብቅ ቁጥጥርም ሊያስፈልግ ይችላል፡፡ ሆኖም ግን የሚኖሩበትን ምድር የሚያደንቁና የሚጠብቁ ሰዎች በጥንቃቄ ከታገዙ በውጪ ሆነው የሌሎችን የዱር ህይወት ለመጠበቅ ከሚፈልጉ በበለጠ ሁኔታ ተፈጠሮን ለመጠበቅ በተግባር የዳበረ አቅም ይኖራቸዋል፡፡ ስለዚህ መልካም አስተዳደር ልማትና ጥበቃን ለማስተዋወቅ ሊረዳ የሚችል በመልካም ተሞክሮዎች የተመሰረተ የአካባቢ ሰዎችን በዘለቄታው መንገድ በድጋሚ ለማስጠቀም የሚችል ህግ ማውጣትን ያካትታል፡፡ የአውሮፓ መማክርት ይህንን መርህ የሚከተል ስምምነት አዘጋጅተዋሉ፡ ለምሳሌ የስደተኛ ዝርያዎች ልማትና ጥበቃ ስምምነት በራፕተረስ የጋርዮሽ ስምምነት ፕሮግራም ላይ እነዚህን መርሆች ለመተግበር እየሰሩ ይገኛሉ፡፡