የአለም የካርበን ዳይ ኦክሳይድና አየር ሙቀት ከቅድመ ኢንዱስተሪ ዘመን በበለጠ ከዓመት ወደ ዓመት እየጨመሩ ናቸው ©  የጋራ ፈጠራ ፡፡
መሬታችን እየሞቀች ነው፡፡ አንድ አንዱ የሙቀት መጨመር በቆይታ በሚከሰተው የፀሃይ መስፋፋትና በመሬት ምህዋር ባሉ አነስተኛ ለውጦች ምክንያት የሚጠበቅ ክስተት ነው፡፡ ሆኖም ግን የዚህ ዓይነቱ ተፅዕኖ ሊገመት የሚችል ሲሆን አሁን የገጠመንን ፈጣን የሙቀት መጨመርን ግን ሊገልፅ አይችልም፡፡ የሰዎች ስልጣኔ እና የጉዞ ልማድ ማደግ ይህን የሙቀት መጨመር ችግር እጅግ አፋጥኖታል፡፡ ከ150 ዓመት በፊት በስዊዲን ሳይንቲስት የአንድ አንድ ጋዞች መጠን መጨመር ከባቢ አየር ብዙ የፀሃይ ሙቀትን እንድታስቀር ያደረጋታል ተብሎ የተገለፀውን ትንበያም እውን አድርጎታል፡፡ ባለፉት ሰባ ዓመታት የጨመረው አስደንጋጭ ሙቀት ምክንያት የአረንጉዴ ጋዞች መጠን መጨመር እንደሆነ ይገለፃል ከነዚህም የአረንጉዴ ጋዞች መካከል በዋነኛነት በብዛት ተከማችተው የሚገኙት ካርበን ዳይ ኦክሳይድና ሚቴን ነው ተብለው ይጠቀሳሉ፡፡
ከአስር አመት በፊት ሐይቁን በሸፈነው በኖርዌይ ብሪስስላንድ ግግርማ ውስጥ የአስራ ሁለት ዓመታት መሸሸጊያ © ፣ ማቲዩሽ ኩርዚክ/ኦሌግ ኮዝሎቭ/ሸተርእስቶክ።
የመሬት ሙቀት መጠን መጨመር ሁለት ዋና ዋና ውጤቶች አሉት፡፡ በጣም ዝግመታዊ ውጤቱ በሰሜን ንፍቀ ክበብ ያለው የበረዶ መቅለጥ ነው፡፡ የአንታረቲካና ግሪንላድ የበረዶ ግግሮች እየቀለጡና በፍጥነት እየፈሰሱ ናቸው፡፡ መሬትን የሸፈኑ በረዶዎችን ተከልለው በባህር ውስጥ ይቀልጣሉ በዚህ ምክንያትም የአለማችን የባህር ወለል በነዚህ መቶ ዓመት በአንድ ሜትር ጨምሮዋል፡፡ የታየው ፈጣኑም ውጤት በባህሮች ሙቀት ለውጥና በዚህ ለውጥ ምክንያት በሚከሰተው የአየር መዛባት ጋር ተያያዥ በሆነው የአየር ንብረት ለውጥ ነው፡፡ ብዙ የውሃ ትነት ከሞቁ ባህሮች ወደ ከባቢ አየር መጨመርና የአካባቢ አየር ለውጥ ለአንድ አንድ ቦታዎች ከሚጠበቀው በላይ ብዙ ዝናብና በረዶ ይሰጣል፡፡ በተቃራኒው ደግሞ ሌሎች ቦታዎች በደረቅ አየርና ውኃ እጥረት ለረዥም ጊዜ የጠቃሉ፡፡
የአየር ንብረት ሲለወጥ ምን ይከሰታል
ጎርፍ በታየላንድ© አቲካን ፖርንቻፕራሲት/ሸተርሰቶክ
ጥሩ የአየር ንብረት በነበራቸው ሚሊዮን ዓመቶች በነበረው ለግብረና ስልጣኔ ምስጋና ይግባውና ሰዎች የህዝብ ቁጥር በጣም ትልቅ ሆኖዋል፡፡ ሆኖም ግን በአሁኑ ሰዓት ያለው የአለም ሙቀት መጨመር ሰዎችንና ተፈጥሮን በአራት መንገዶች ያሰጋል ይኸውም በጎርፍ፣ እሳት፣ ረሃብና በሽታ ናቸው፡፡ በዝቅተኛ ስፍራዎች ላይ የባህሮች መጨመርና አፈርን አጥቦ ወደ ሌላ ቦታ በሚወስድ ከባድ ዝናብ ጎርፎች ይባባሳሉ፡፡ የረዥም ጊዜ ደረቅ አየር አትክቶች እነዲደርቁና በሰደድ እሳት እንዲቃጠሉ ያደርጋቸዋል፡፡ ድርቅና ጎርፍ ሰዎችና እነስሳት የሚመገቡአቸውን አትክልቶች ያጠቃሉ ይህም በመጠጥ ውኃ እጥረት የሚባባሰውን ረሃብን ያስከስታል፡፡ እነኚህ ውጤቶች ደግሞ እንስሳትንና እፅዋትን በአዲሱ ሞቃታማ የአየር ንብረት ወደ ሰሜናዊ ንፍቀ ክበብ የሚስፋፋው በሞቃታማ አካባቢ የሚገኙ በሽታዎች ተጋላጭ ያደርጋቸዋል፡፡
ሰደድ እሳት በአሜሪካ© ARM/ሸተርሰቶክ
የተቀበሩ ነዳጆች፡ ከሰል ድንጋይ፣ ዘይትና፣ ጋዝ መቃጠል መጨመር የካርበን ዳይ ኦክሳይድ መጠንን ይጨምራል፡፡ እነኚህን ነዳጆች ማቃጠል ብናቆምም አሁን ላይ እየጨመረ ያለውን የሙቀት ወደ ቦታው ለመመለስ ብዙ ዓመታት ይፈጃል፡፡ በጣም አስከፊው ችግር ደግሞ የሙቀት መጠኑ ለመመለስ አስቸጋሪ ወደሆነበት የመጨረሻው ጫፍ ሊጨምር መጫሉ ነው፡፡ ይህ ደግሞ በሞቃታማ አካባቢ የሚገኙ ሰፊ ደኖችን ማጥፋት እጅግ በጣም አሳሳቢ ያደርጉታል፡፡ ሌሎች የደን ቦታዎች በሰደድ እሳት እና አፈር በድርቅ ከጠፋ የአካባቢው ሰው የግድ ወደ ሌላ በታ ይንቀሳቀሳሉ፡፡ የባህር ወለል መጨመር በውኃ የተከበቡ ከተሞችን በጎርፍ እንዲጥለቀለቁ ካደረገ ብዙ ሰዎች ይሰደዳሉ፡፡ የዚህ ዓይነቱ ስደት አደጋ የአለም-ዓቀፍ ትኩረት ይስብና ከአየር ንብረት ለውጥ፣ ተፈጥሮ ልማትና ጥበቃ እና እራሳችንን ከመታደግ መፍትሄዎች ሙሉ በሙሉ ሊያርቀን ይችል ይሆን?
ምን ማድረግ እንችላለን?
አዲስ የቤት ውሰጥ የኃይል አቅርቦቶች በአውሮፓና በአፍሪካ© ፣ሄኪ61/አቶ ኖቬል/ሸተርሰቶክ
ባህሮችን፣ አፈሮችንና እፅዋቶችን ብዙ ካረበን በውስጣቸው እነዲያቁሩ ለማገዝ ተፈጥሮአዊ መፍትሄዎች አሉ፡፡ ዛፎችን በሰፊው መትከል የአፈርን ለምነት ያድሳል በተጨማሪም በህንፃዎች ላይ በሚገኙ የእንጨት ውጤቶች ላይ ካረበንን ለማቆር እድል ይሰጣል፡፡ ስነምህዳራዊ መሰተጋብርን በለም፣ አዲስ ደንና እየታደሰ ባለ ግብርና መሬት ላይ እንዲያገግም በማድረግ የአፈርን እረጥበት መመለሰ በብዙ ሊረዳ ይችላል፡፡ ሌሎች መፍትሄዎችም አሉ፡፡ በፀሀይ እና ንፋሰ ኃይል የሚመነጩ የኤሌትሪክ ኃይሎች ለቤቶች፣ ኢንዱስትሪ፣ እና ትራንሰፖርት በቂ ኃይል ሊናጠራቅምበት የምንችልበትን መንገድ በማግኘት የነዳጅ ኃይልን ተክቶ እነዲያበራ ማድረግ ይቻላል፡፡