ስለ አሳታሚዎች

የኛ ጥረት በባለሙያዎች የተደገፉ ናቸው  እናም የዱር ሀብቶችን በዘለቄታዊ መንገድ በመጠቀማችን ደስተኞች ነን፡፡
የኛ ጥረት በባለሙያዎች የተደገፉ ናቸው እናም የዱር ሀብቶችን በዘለቄታዊ መንገድ በመጠቀማችን ደስተኞች ነን፡፡

ይህ ድህረ-ገፅ የአለም ዓቀፍ ተፈጥሮ ልማትና ጥበቃ ህብረት ድርጅት (International Union for Conservation of Nature (IUCN)) ውጤት ነው፡፡ ይህ ድርጅት የተመሰረተው በ1941 ዓ.ም. ሲሆን በአሁኑ ጊዜም በ84 ሀገራቶች ከ1100 በላይ ከሚሆኑ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጋር የዚህ ህብረት አባላት ናቸው፡፡ IUCN በተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ህብረት ውስጥ በብዘሀ-ህይወት፤ ተፈጥሮ ልማትና ጥበቃ እና በዘለቄታዊ የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀም ላይ በዋነኛነት የሚሰራ ብቸኛው አለም ዓቀፍ ታዛቢ ድርጅት ነው፡፡

 

በዚህ ገፅ የሚገኘው ፅሁፍ መረጃው የ Species Survival Commission እና Commission on Environmental Economic and Social Policy አጋር ድርጅት እነዲሁም እህት ድርጅታችን በሆነው የዘለቄታዊ ጠቀሜታ እና የገቢ ምንጮች እርዳታ ተሰብስቦ በIUCN ከሚገኘው ከስድስቱ አንዱ በሆነው የስነምህዳራዊ መሰተጋብር አያያዝ ኮሚሽን ከስነምህዳራዊ መሰተጋብር ዘለቄታዊ አጠቃቀምና አያያዝ (Sustainable Use and Management of Ecosystems) በተውጣጡ 500 ባለሙያዎች ሰምምነት በመጀመሪያ በእነግሊዘኛ ተፅፎ ከዚያም በተለያዩ ቋንቋዎች ተተረጎመ፡፡ የዚህ ጣቢያ የመረጃ መረብም የሚመራው በአህጉራቶችና በሃገራት ደረጃ በሚገኙ የIUCN ባለሙያዎች ነው፡፡

 

በመሆኑም ይህን ገፅ ማንበብ የተፈጥሮአዊ አለም ገፅታና በአለማችን ከዱር ፍጥረታት ጋር ጥብቅ ቁርኝት ያላቸውን የተለየ አስተዋፅኦ ያበረከቱትን ሰዎችን ማወቅና መረዳት ያስችላል ብለን ተስፋ እናደርጋለን፡፡ በተጨማሪም በእርስዎ ቋንቋ ከሌሎች የመረጃ ሰጪ ገፆች ጋርና በጉዳዩ መንደርደሪያ ሃሳቦችን ከሚሰጡ ገፆች ጋር እናገናኞታለን፡፡ ሰለዚህም ከተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ለተገኙ ለተፈጥሮ ሀብት ልማትና ጥበቃ አመርቂ ውጤቶች መልካም ዜና አዕምሮአችን ክፍት እናድርግ ይህ ሲሆን እስከአሁን ስኬታማ የሆኑ ሃሳብና ጥረቶች በቀላሉ ለሰፊው ህዝብ ይዳረሳሉ፡፡ ይህንን ከተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች የተገኘውን እውቀት በመውሰድ አግባባዊ በሆነ መንገድ በእረስዎም አካባቢ ላይ እንዲተገብሩት በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

በእነዚህ ገጾች ላይ ያሉት ጭብጦች ዓላማ እናንተን ለማበረታታት ነው: